I

Improvise : (ኢምፕሮቫይስ) - ያለ እቅድ ቅርብ ባለ እቃ ተጠቅሞ ማዝጋጀት፤ መስራት፤ እንደምንም ብሎ ማዘጋጀት።
I was not expecting you so soon; I will have to improvise something for lunch
ቶሎ ትመጣለህ ብየ አልጠበቁም፤ እስቲ ያለውን ፈልጌ ጠባብሼ ምሳ ልስራለህ።


Due to our limited budget and resources, we are required to improvise.

መጠነኛ ገንዘብና የ ሰው ሃየል ስላለን በተቻለን መጠን እንደምንም ብለን መስራት ይኖርብናል።

Impenitent : (ኢንፐነተንት) ላደረጉት መጥፎ ስራ ወይም በደል አለመቆጨት፤ አለመጸጸት፤ አጥፍቻለሁና ይቅርታ አድርጉልኝ የማይል። ሃጥያቱን የማይናዘዝ።
What happens if we die impenitent?
ሃጥያታችንን ሳንናዘዝ ከሞትን ምን ይደርርስብናል?

Impetuous: ኢም-ፕ-ቹ-ወስ ፡ ቀልቃላ ፤ ችኩል ፤
His impetuous decisions brought the company to its final days.

Importunate : (ኢምፖርቹኔት) ጨቅጭቆ መለመን፣ መጠየቅ፣ እየጠይቁ ወይም እየለምኑ ሰውን ማሰልችት።
The importunate demands of the Jehovah Witnesses to come into my house is getting on my nerves.

Impressionable : (ኢም-ፕሬስ-ሺን-አብለ) በቀላሉ የሚታለል፣ የሚሞኝ፣ታቡላራዛ ።
MTV is provocative programming designed to exploit young,impressionable kids.
የኤምቲቪ ቀስቃሽ ፕሮግራም ወጣትና ታቡላራዛዎችን መጠቀሚያ ኢላማ የሚያደርግ ነው::


Incommensurate : (ኢን - ኮም- ሜን-ሱሬት) ፡ መጠኑ ያልተስተካከለ፤ጎዶሎ፤ ከሚገባው በታች የሆነ።
I was rewarded incommensurate with my efforts.
የልፋቴን ያሀል አልተከፈለኝም

Inconvertible : (ኢን-ኮን-ቨርት-ኢ-ብል) የማይሻር፣ የማይለወጥ፣ የማያጠራጥር ሃቅ
“The truth is incontrovertible, malice may attack it, ignorance may deride it, but in the end; there it is.” - Winston Churchill

"እውነት አትሻርም ፤ ክፋት ልታጠቃት ፤ ድንቁርና ልታላግጥባት ትችላለች፤ በመጨረሻ ግን እሷው ፍንክች::"
-ዊንስተን ቸርችል


Indecorous : (ኢን-ዴ-ኮ-ረስ) ስነስራዓት የሌለው ፤ አግባቢ ያልሆነ፤ ነውር፤ አስቀያሚ ፤ ከባህል ወይም ከልምድ ውጭ የሆነ።
Please don't interpret my open criticism as indecorous.
እባክህን ግልጽ ሂሴን ከድፍረትና ብልግና አትቁጠርብኝ::

Infallible : (ኢንፋልብል ) የማይሳታት፣ እርግጠኛ፣ ፍጹም ፤ ትክክል፤ ቀትተኛ።
Example = the infallibility of the truth can not be denied.
ምሳሌ = የ ሃቁን ፍጹምነት ሊካድ አይቻልም::


Innocuous : (ኢ-ኖክ-ዩ-ወስ)፡ የማያስቀይም፣ የማይጎዳ፣የማያናድድ። (በተለይ ወሬ)
But that seemingly innocuous decision can produce fatal results.
ይሄ ላዩን ሲታይ ጤነኛ የሚመስል ውሳኔ መጨረሻው ላያምር ይችላል::

Inspire : (ኢንስፓየር) የሃሳብ፣ የ መንፈስ ፣ የ ሞራል ተስፋ መስጠት
Example = You inspire me to achieve my goals
ምሳሌ =
አላማዬን እንዳሳካ የ ተስፋ እርዳታ ካንተ(ካንቺ) አገኛለሁ

Intermittent : አንዳንዴ፣ አልፎ አልፎ፣ የ ሚቆራረጥ።
Example = my car makes a clanking intermittent sound.
ምሳሌ = ምኪናዬ አንዳንዴ የሚቆራንቆር ድምጽ ያሰማል።

Integrity: (ኢንተግሪቲ) ቅንነት፣ ጽንነት፤ የማይወላውል ቅኑ ስነስራዓት፤ ጠንካራ የግብረገብ እምንነት ።
His leadership clearly lacks integrity.
አመራሩ ቅኑ ግብረገብ እንደሌለው በግልጽ ያስታውቃል።

Intolerable
: (ኢንቶለሬብል) ሊታገሱት የማይቻል ስቃይ፤ ስድብ፤ ጫጫታ፤ ዛቻ።
Exampe = His threats are intolerable.
ምሳሌ = ዝቻውን ልታገሰው አልችልም።

Invidious
: (ኢንቪድየስ) ጥላቻ ወይም ቅያሜ ሊያስነሳ የሚችል ነገር፤ አላግባብ ሆኖ የሚሰማ።
I am deeply angered by your invidious accusation.
እኔን በጥላቻ መወንጀልሽ በጣም አናዶኛል።

invidious discrimination
ያላግባብ ማዳላት።